AMN-ጳጉሜን 2 /2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባን ገጽታ በአዲስ መልክ የቀረጹት ሜጋ ፕሮጀክቶች እና የኮሪደር ልማቶች የከተማዋን ውበት ከማሳደግ ባለፈ የዕለት ተዕለት የነዋሪዎችን ኑሮ በቀጥታ ያሻሻሉ እና ለሀገራዊ ማንሠራራት መሰረት የጣሉ ናቸው፡፡
አገልግሎትን በቴክኖሎጂ በማዘመን የዲጂታል አስተዳደርን እውን ያደረጉ እንዲሁም የህዝብን እንግልት የቀነሱ የመሶብ የአንድ ማዕከል ስራዎች፣ የኑሮ ውድነትን ለማቃለል የታለሙ የገበያ ማዕከላት ግንባታዎች፣ አረንጓዴ የመዝናኛ ቦታዎች መስፋፋት፣ የአቅመ-ደካሞች የቤቶች እድሳት እና የተጠናከሩ የበጎ አድራጎት ስራዎች የከተማዋን ማህበራዊ መስተጋብር በማጠናከር የኢኮኖሚና ማህበራዊ ተጠቃሚነትንም ከፍ አድርገዋል፡፡
የተከናወኑት የኮሪደር ልማት እና የከተማ ማሻሻያ ፕሮጀክቶች የከተማዋን የትራፊክ ፍሰት በማሳለጥ፣ ለእግረኞች ምቹ የሆኑ ንጹህ እና ደህንነታቸው የተጠበቁ መንገዶችን ፈጥረዋል።
አገልግሎት አሰጣጥን ከወረቀት ንክኪ ነጻ በማድረግ እና በዲጂታል ቴክኖሎጂዎች የተደገፉ ፈጣን፣ ግልጽና ተደራሽ የመንግስት አገልግሎቶችን በመዘርጋት የዜጎችን እንግልት ሊያስቀሩ የሚችሉ ስራዎችም ተከናውነዋል።
አዳዲስ ማህበራዊና አረንጓዴ የመዝናኛ ቦታዎች መገንባታቸው የነዋሪዎችን ማህበራዊ መስተጋብር አጠናክሮ የኑሮ ደረጃን ከፍ አድርጓል።
የተሻሻሉ አካባቢዎች ለንግድ እና ለቱሪዝም እንቅስቃሴ ምቹ ሁኔታን በመፍጠር የሥራ ዕድል ፈጠራንና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን አጠናክረዋል።
በፍሬሕይወት ብርሃኑ