የሃገር መከላከያ ሠራዊት የሉዓላዊነት መከታና የአይበገሬነት ተምሳሌት ነዉ

You are currently viewing የሃገር መከላከያ ሠራዊት የሉዓላዊነት መከታና የአይበገሬነት ተምሳሌት ነዉ

AMN – መስከረም 8/2019 ዓ.ም

የሃገር መከላከያ ሠራዊት፤ ሀገሪቱን ከማንኛውም የፀጥታ ስጋት ለመከላከል በቴክኖሎጂ፣ በሰው ኃይል እና በመሣሪያ የተደራጀ የሉዓላዊነት መከታና የዘመኑ የአይበገሬነት ተምሳሌት ነዉ።

ከለውጡ ዓመታት ወዲህ በተደረጉ ስልታዊ የመዋቅር፣ የቁሳቁስ እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎች ሰራዊቱ ዘመኑን የሚመጥን አቅም መገንባት ችሏል።

በዘመናዊ ወታደራዊ ሳይንስ፣ በስነ-ልቦና እና በዲሲፕሊን የታነጸ የህዝብንና የሀገርን ደህንነት ከሁሉም በላይ በሚያስቀድም ቆራጥ ተቋም ሆኖ ተደራጅቷል።

ሀገራዊ ደህንነትን አስቀድሞ ለመጠበቅ የሚያስችሉ ዘመናዊ የዲጂታል መረጃ መረቦች፣ የራዳር እና የክትትል ቴክኖሎጂዎች እንዲሁም የሳይበር መከላከያ ስርአቶችንም ገንብቷል።

ከዚህም በተጨማሪ የአየር ክልልን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ዘመናዊ የጦር አውሮፕላኖችና ድሮኖችን በመጠቀም ሰራዊቱ በየትኛውም መልክዓ ምድር ተልዕኮውን በብቃት መወጣት በሚያስችል ዝግጁነትና ቁመና ላይ ይገኛል።

የሀገሪቱን ሉዓላዊነት፣ ድንበር እና ብሄራዊ ጥቅም ማስከበር የሰራዊቱ ዋንኛ ዓላማ ሲሆን፤ ይህንን ታሪካዊና ህዝባዊ አደራ ለመወጣት በተለያዩ ግንባሮችና ስትራቴጂካዊ መስኮች በተጠንቀቅ እየሰራ ይገኛል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎችን በብቃት እየተወጣ የሚገኝ አስተማማኝ ሃይል ነዉ።

ኢትዮጵያ በረጅሙ የታሪክ ጉዞዋ ነፃነቷን፣ ሉዓላዊነቷንና ህልውናዋን በመስዋዕትነት አስጠብቀው ያለፉ ጀግኖችን የፈጠረች ሀገር ስትሆን፣ የአድዋ ድል ለዚህ ህያው ማሳያ ነው።

የዚህ ታሪክ ተተኪ የሆነው የዛሬው የሃገር መከላከያ ሠራዊት የትናንቱን ጀግንነት በዘመኑ ሙያዊ ብቃት፣ በቴክኖሎጂ: በጠንካራ ስነ-ምግባር እና በህግ የበላይነት መርህ እያረጋገጠ ይገኛል።

ሰራዊቱ አሁን ላይ የተሰጠዉን ማንኛዉንም ግዳጅ በአስተማማኝ መልኩ በአጭር ጊዜ ዉስጥ የመፈጸም ደረጃ ላይ መገኘቱ ለአይበገሬነቱ ትልቅ ማረጋገጫ ነዉ።

በበረከት ጌታቸው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review