ኢትዮጵያ በታሪኳ እና በህዝቦቿ ጽናት የቀጣናው ምሰሶ ሆና የቆየች ሀገር ናት

AMN- መስከረም 11/2019 ዓ.ም

ኢትዮጵያ በረጅም ዘመናዊና ጥንታዊ ታሪኳ፣ በጂኦፖለቲካዊ አቀማመጧ እንዲሁም በህዝቦቿ ጽናት የቀጣናው ምሰሶ ሆና የቆየች ሀገር ናት።

ቅኝ ግዛትን በመቋቋም ለአፍሪካ ነጻነት ተምሳሌት ሆናም የኖረች ሀገር ናት ኢትዮጵያ።

በርካታ ብሔር ብሔረሰቦች በጋራና በመከባበር የሚኖሩባት የሰላም እና የፍቅር ምድር ኢትዮጵያ የተለያዩ እምነቶች እና ባህሎች መገኛ ናት።

የኢትዮጵያ ታላቅነት የሚረጋገጠው በጠንካራ ሉዓላዊነት፣ በሰላማዊ የዲፕሎማሲ ግንኙነቶች እንዲሁም ለቀጣናው እድገት በሚደረጉ አዎንታዊ ትብብሮችም ጭምር ነው።

የኢትዮጵያ ፈጣን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እና የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄዎችም እጅግ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ይገኛሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከዚህ ቀደም ባስተላለፉት መልዕክት፤ የኢትዮጵያ ታላቅነት በታሪኳ ብቻ ሳይሆን በዛሬ ሥራዋና በነገ ራዕይዋ ይገለጣል ብለው ነበር፡፡

በጋራ ስንሠራ፣ በጋራ ስንተማመን እና በጋራ ስንቆም ኢትዮጵያ እንደምትችልም አንስተዋል፡፡

በእያንዳንዳችን መስዕዋትነት፣ጥረትና ትጋት ላይ ኢትዮጵያ አሸንፋ ትቀጥላለች ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

የሻምበል ምህረት

See less

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review