የሕዳሴ ግድብ ድል ሌሎች ግዙፍ ፕሮጀክቶችን አቅዶ ለመፈጸም አቅም ሆኗል

AMN- መስከረም 24/2019 ዓ.ም

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በኢኮኖሚ፣ በቴክኖሎጂ እና በዲፕሎማሲ መስኮች የሃገሪቱን ታላቅነት የሚያሳዩ ሌሎች ግዙፍና ትውልድ ተሻጋሪ ፕሮጀክቶች እንዲፈጠሩ መሰረት ጥሏል።

የታላቁ የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት መጠናቀቅ የኢትዮጵያ እጆች ሲተባበሩ ሀገራዊ ግቦችን ከፍ አድርጎ ማሳካት እንደሚቻል የተግባር ምስክር ሆኗል፡፡

ኢትዮጵያውያን አቅማቸውን አስተባብረው አኩሪ ታሪክ መሥራት እንደሚችሉ በዚህ የልማት አርበኝነት በተግባር አሳይተዋል።

የመተባበርን ትልቅ ኃይል ለቀጣዩ ትውልድና ለአፍሪካውያን በማስተማርያ ኢትዮጵያውያን በአንድነት ከቆሙ ፈተናዎችን አልፈው የማያሳኩት አንዳችም ነገር እንደሌለ ምስክርም ሆኗል፡፡

ከታላቁ የህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ በኋላ የኢትዮጵያን ከፍታና ሁለንተናዊ እመርታ የሚያሳዩ የተለያዩ ውጤታማ ፕሮጀክቶችን ከቃል ወደ ተግባር መለወጥ ተችሏል፡፡

ፕሮጀክቶቹ በግብርና፣ በመንገድ፣ በቱሪዝምና በሌሎች ዘርፎች የተከናወኑ ሲሆን ግንባታቸውን በጊዜና በጥራት ተግባራዊ ማድረግም ተችሏል፡፡ ይህም የኢትዮጵያውያን የማድረግ አቅም በተግባር ያሳየ ነው፡፡

መዲናዋን አዲስ አበባን ጨምሮ በበርካታ ክልል ከተሞች የተከናወኑ እና እየተከናወኑ ያሉ የኮሪደር ልማት ሥራዎች፣ የከተሞችን ገጽታ በመቀየር ማራኪ፣ ለኑሮ ምቹ እና ለቱሪዝም ተስማሚ እንዲሆኑ አድርገዋል።

ፕሮጀክቶቹ የሀገር ውስጥ አቅምን በማቀናጀት፣ በፍጥነት እና በጥራት እንዲገነቡ በመደረጉ የኢትዮጵያውያንን የሥራ ባህልና ትጋት ከፍ አድርገዋል።

እነዚህ ፕሮጀክቶች እንደ ህዳሴ ግድቡ ሁሉ “እንችላለን” የሚለውን የኢትዮጵያውያን እሳቤ እውን ያደረጉ ሲሆን የነገዋን የበለጸገች ኢትዮጵያ የመገንቢያ መሠረት እየጣሉ ይገኛሉ።

የሻምበል ምህረት

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review