የሉዓላዊነት ጋሻ እና የህዝብ አለኝታ፤ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት

AMN- መስከረም 24/2019 ዓ.ም

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የአንድ ሀገር ወታደራዊ ተቋም ብቻ ሳይሆን የረጅም ጊዜ የሉዓላዊነት ታሪክ፣ የነጻነት ጋሻ እና የህዝቦች አብሮነት ማሳያ የሆነ የአይበገሬነት ማማ ነው።

ሠራዊቱ በፈተናዎች ሳይበገር የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት አጽንቷል።

የመከላከያ ሰራዊት ከትናንት እስከ ዛሬ ባለው የጸና አቋሙ እና በውጊያ ብቃቱ የሀገሪቱን ታሪካዊ ክብር አስጠብቋል፡፡

የሀገሪቱን ጂኦፖለቲካዊ አቀማመጥ እና ጫናዎችን ተቋቁሞ፣ የውጭ ጠላቶችን መመከት ብቻ ሳይሆን የውስጥ አንድነትን በማስጠበቅ ረገድ ሠራዊቱ የማይተካ ሚና አለው። ሠራዊቱ የህዝብ ልጅ በመሆኑ በህዝብ ፍቅር እና ድጋፍ የቆመ ነው።

ሀገርን ከሁሉ በላይ ማስቀደም እና ለዜጎች ደህንነት ሲባል የከፈለውና እየከፈለ ያለው መስዋዕትነት የሠራዊቱን ሞራል የማይበገር አድርጎታል።

የኢትዮጵያን ድንበርና ሉዓላዊነት በማንኛውም ዋጋ የማስጠበቅ ቆራጥነት የሠራዊቱ መለያ ምልክትም ነው።

በወቅቱ ያለው ዓለም አቀፍና ቀጣናዊ ሁኔታ በሚጠይቀው ልክ ሰራዊቱ ዝግጁነቱን በማሳደግ የሀገሪቱን ጥቅም አስጠብቆ ቀጥሏል፡፡

መከላከያ ሠራዊቱ በየጊዜው በሚደረጉ አዳዲስ ማሻሻያዎችና የአቅም ግንባታ ስራዎች ራሱን በማብቃት ላይም ይገኛል።

ሠራዊቱ ካለው ታሪካዊ የውጊያ ልምድ ጋር ዘመናዊ የውጊያ ስልቶችን እና ቴክኖሎጂዎችን በማቀናጀት ከጊዜ ወደ ጊዜ ብቃቱንም እያጎለበተ ነው።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የኢትዮጵያዊነት ምሰሶ፣ የህዝቦች ሰላም ዋስትና እና የሀገር ፍቅር መገለጫ ነው።

በፍሬሕይወት ብርሃኑ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review