ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ጋር ተወያዩ

AMN-ጥቅምት 4/2019 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ጋር በስልክ ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ጋር በሁለትዮሽ፣ በቀጣናዊ እና በባለብዙ ወገን የጋራ ትኩረትን በሚሹ ጉዳዮች ላይ እጅግ ፍሬያማ የሆነ የስልክ ውይይት አድርጌያለሁ ብለዋል፡፡

ያካሄድነው ውይይት በኢትዮጵያና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል ያለውን እድሜ ጠገብ ወዳጅነት ወደ ላቀ ስትራቴጂካዊና ተግባራዊ አጋርነት ለማሳደግ በሁለቱም አገራት በኩል ያለውን ቁርጠኝነት ማረጋገጫ ነው ሲሉም ገልጸዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ቀጣይነት ያለው ድጋፍ በተመለከተ የሰጠችውን ማረጋገጫም አድንቀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፤ የሁለትዮሽ ትብብራችንን ለማጠናከር እንዲሁም በቀጣናዊና ባለብዙ ወገን መድረኮች ቅድሚያ በምንሰጣቸው የጋራ ጉዳዮች ላይ አብረን ለመሥራት ያለንን ቁርጠኝነት አረጋግጣለሁ ብለዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review