AMN-ጥቅምት 4/2019 ዓ.ም

በሴካፋ ከ17 ዓመት በታች አፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የምድብ ሁለተኛ ጨዋታውን ከዩጋንዳ ጋር ያደረገው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን 1ለ1 ተለያይቷል።
ዘሚካኤል ምንኣህል ኢትዮጵያን መሪ ያደረገች ግብ ቢያስቆጥርም ዩጋንዳ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ የአቻነት ግብ አግኝታለች።

በመጀመሪያ ጨዋታ ብሩንዲን 3ለ0 የረታችው ኢትዮጵያ አራት ነጥብ በመያዝ ከዩጋንዳ በግብ ክፍያ ተበልጣ 2ኛ ደረጃ ይዛ ምድቧን አጠናቃለች። ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ ግማሽ ፍፃሜ መቀላቀሏን አረጋግጣለች።
በሸዋንግዛው ግርማ