ልዩነታችንን አክብረን፣ አቅማችንን አቀናጅተን፣ በመደመርና በትብብር የጋራ ብልጽግናን እንገንባ – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing ልዩነታችንን አክብረን፣ አቅማችንን አቀናጅተን፣ በመደመርና በትብብር የጋራ ብልጽግናን እንገንባ – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN- ጥቅምት 22/2019 ዓ.ም

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማኅበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ በዓለማየሁ አረዳ (ዶ/ር) የተጻፈውን “ምሉዕነት” የተሰኘ መጽሐፍ አድንቀዋል።

መጽሐፉ የግለሰብን ውስጣዊ እድገት ከማኅበረሰብ ጥንካሬ ጋር በማገናኘት፤ አካታች ፖለቲካን፣ የጋራ ብልጽግናንና ባህላዊ ብዝሃነትን የሚያቀናጅ ጥልቅ ሐሳብ ያቀርባል።

የሥራው ዋና መልዕክትም ልዩነታችንን የመለያየት ምክንያት ሳይሆን የጥንካሬ ምንጭ አድርገን፣ በመተማመን፣ በትብብርና በመደመር የወደፊት ዕድላችንን በጋራ መገንባት እንዳለብን የሚያስገነዝብ መሆኑ ገልፀዋል።

ይህም ግብ በመንግሥት ብቻ ሳይሆን፣ በሁሉም ዜጎች የጋራ ኃላፊነትና ተሳትፎ የሚሳካ በመሆኑ፣ መጽሐፉ ለሀር የጋራ እውቀትና ለተሻለ ማኅበረሰብ ግንባታ ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋል ብለዋል።

ከንቲባ አዳነች፤ ልዩነታችንን አክብረን፣ አቅማችንን አቀናጅተን፣ በመደመርና በትብብር የጋራ ብልጽግናን እንገንባ በማለት ለዶክተር ዓለማየሁ አረዳ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review