ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከአረብ ቡድን የልዑካን መሪዎች ጋር ተወያዩ

AMN- ኅዳር 2/2019 ዓ.ም

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የCOP32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ማዕቀፍ ስምምነት (UNFCCC) ስር የሚገኙ የአረብ ቡድን አባል ሀገራት የልዑካን መሪዎች ስብሰባ ላይ በመገኘት ንግግር አድርገዋል።

በስብሰባው ወቅት የአረብ ቡድን አባል ሀገራቱ ኢትዮጵያ በሚኖራት አመራር እንዲሁም ተመራጭ ፕሬዚዳንቱ በCOP32 ሂደት ላይ በሚያሳዩት መሪነት ላይ ያላቸውን ሙሉ እምነት ገልጸዋል።

አባላቱ አክለውም በኢትዮጵያና በአረብ ቡድን ሀገራት መካከል ያለው ታሪካዊና ጠንካራ ግንኙነት የበለጠ እየጎለበተ መምጣቱን ጠቁመዋል።

ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ ከተሳትፎ አድራጊ አካላት እና ከሁሉም ተዋዋይ ወገኖች ጋር በቅርበት በመሥራት ውጤታማና የተሳካ የCOP32 ጉባኤን ለማካሄድ ሙሉ ቁርጠኝነትና ዝግጁነት እንዳላት ለልዑካን መሪዎቹ አረጋግጠዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review