AMN ኅዳር 7/2019 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የCOP32 ዝግጅቶችን በመገምገም ሥራዎች የሚመሩበትን ስትራቴጂካዊ አቅጣጫ መስጠታቸዉን ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት
ዛሬ ጠዋት COP32 የብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴን በመሰብሰብ አጠቃላይ የሥራ ሂደቱን ገምግመናል ብለዋል፡፡
ዝግጅቶችን ከፈትሽን በኋላም ሥራዎች የሚመሩበት ስትራቴጂካዊ አቅጣጫ ሰጥቻለሁ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉባኤውን በስኬት ለማስተናገድ ሁሉም ግብረ-ኃይሎች ተናብበው እንዲሠሩ በማድረግ፣ የተቀናጀ ሁሉን አቀፍ የመንግሥት አካሄድ መከተል ወሳኝ መሆኑን በአጽንኦት አሳስቤያለሁ ብለዋል፡፡
COP32 ታላቅ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ከመሆኑ ባለፈ፣ የኢትዮጵያን የአየር ንብረት እና የአካባቢ ጥበቃ አጀንዳን ለማራመድ፣ አጋርነትን ለማጠናከር፣ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ እንዲሁም ብሔራዊ ጥረቶቻችንን ወደ ዘላቂ ውጤት ለመለወጥ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መልእክት አስተላልፈዋል፡፡