ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት ዓመታት የሀገርን ብልጽግና እውን ለማድረግ በርካታ ሰው ተኮር የልማት ስራዎችን አከናውኗል፡-የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፖርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

You are currently viewing ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት ዓመታት የሀገርን ብልጽግና እውን ለማድረግ በርካታ ሰው ተኮር የልማት ስራዎችን አከናውኗል፡-የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፖርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

AMN – ጥር 7/2017 ዓ.ም

ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት ዓመታት የሀገርን ብልጽግና እውን ለማድረግ በርካታ ሰው ተኮር የልማት ስራዎችን ማከናወኑን የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፖርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡

የክፍለ ከተማው ብልጽግና ፖርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፓርቲውን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ቅድመ ኮንፍረንስ አካሂዷል።

በኮንፍረንሱ ላይ ፓርቲው ባለፉት ዓመታት የሀገርን ብልጽግና እውን ለማድረግ በርካታ ሰው ተኮር የልማት ስራዎችን ማከናወኑን የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ መብራቱ ደሴ ተናግረዋል፡፡

ፓርቲው እስካሁን ግዙፍ ፕሮጀክቶችን በአጭር ጊዜ ውስጥ በማከናወን አስደማሚ ተግባራትን አከናውኗልም ብለዋል።

የፓርቲውን 2ኛ ጉባኤ ስናካሄድም እንደ ክፍለ ከተማ ያልተከናወኑ ተግባራትን ዳግም በመፈተሽ ህዝባችንን የበለጠ ለማገልገል ቃል የምንገባበት ነው ብለዋል።

በአለሙ ኢላላ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review