ኢትዮጵያ እና ኳታር የሁለትዮሽ ውይይት አደረጉ

You are currently viewing ኢትዮጵያ እና ኳታር የሁለትዮሽ ውይይት አደረጉ

AMN – የካቲት 24/2017 ዓ.ም

በኳታር፣ የመንና ኢራን የኢትዮጵያ አምባሳደር ፈይሰል አልይ ኢብራሂም በኳታር ሹራ ካውንስል የኳታር ፓርላማ ወዳጅነት ኮሚቴ ሊቀመንበር ሳድ ቢን አህመድ አል-ሚስናድ ጋር ውይይት አድርገዋል።

ውይይቱ የኢትዮጵያ እና የኳታርን የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ግንኙነቶችን ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው።

የሀገራቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በየሀገራቱ የሥራ ጉብኝት ማድረግ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መነጋገራቸውንም በዶሃ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review