ለሶስት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆየው የብልጽግና ፓርቲ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ተጠናቀቀ

You are currently viewing ለሶስት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆየው የብልጽግና ፓርቲ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ተጠናቀቀ

AMN – የካቲት 29/2017 ዓ.ም

ለሶስት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆየው የብልፅግና ፓርቲ የ6 ወራት የስራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ተጠናቋል፡፡

በሶስት ቀናት የግምገማ መድረክ የፓርቲ ሥራዎች አፈጻጸም ውጤታማነት በጥልቀት መገምገም መቻሉም ተመላክቷል፡፡

በመድረኩ የጠንካራ ፓርቲ፣ ጠንካራ መንግስት እንዲሁም ጠንካራ ሀገር የመገንባት ግቦችን መሰረት በማድረግ ባለፉት 6 ወራት ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸው የተጠቆመ ሲሆን፣ ቀጣይነቱን ማረጋገጥ እንደሚገባም መግባባት ላይ መድረሱ ተጠቁሟል።

ባለፉት ወራት የፖለቲካ፣ የአደረጃጀት እና የሕዝብ ንቅናቄ ስራዎች አፈጻጸም በጥልቀት በመገምገም ስኬቶችን ማስቀጠል እንደሚገባም ተገልጿል።

ስኬቶችን ለማስቀጠል፣ ክፍቶችን ለመሙላት እንዲሁም ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉም ተጠቁሟል።

በግምገማው በፓርቲው መዋቅር ግንባር ቀደም ተሣትፎ የሚከናወኑ የንቅናቄ አጀንዳዎች ላይ በመምከር የቀጣይ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል ተብሏል።

የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ፣ ክህሎት መር የስራ ዕድል ፈጠራን ለማሳደግ እንዲሁም ከተረጂነት መላቀቅ ሀገራዊ ግብን ለማሳካት የተሰሩ ውጤታማ ስራዎችን ማስቀጠል እንደሚገባ መግባባት ላይ መደረሱን ከብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review