በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የሚገኙ የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ባለሙያዎች በአዲስ አበባ ከተገነቡ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች መካከል የካዛንቺስ ኮሪደር ልማትን ጉብኝተዋል::
ባለሙያዎቹ “የተደራጀ ኮሙኒኬሽን እና ሚዲያ የሀገራዊ መግባባት ካስማ ፤የትውልድ ግንባታ መሠረት ነው” በሚል መሪ ሃስብ ነው እየጎበኙ የሚገኙት ::
በመዲናዋ ባለፉት ጥቂት አመታት የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ እና የመዲናዋን ገፅታ የቀየሩ የልማት ስራዎች መሠራታቸዉን የገለፁት የሚዲያ ባለሙያዎቹ ለዚህ ደግሞ የካዛንቺስ የኮሪደር ልማት ማሳያ ነዉ ብለዋል ::
በመዲናዋ የተገነቡ የልማት ስራዎች ለመጭዉ ትዉልድ እንዲሸጋገሩ የበኩላቸዉን ሚና እንደሚወጡ ተናግረዋል