አሜሪካ የጦር መሳሪያዎችን ሕዋ ላይ ልትገጥም ነው

You are currently viewing አሜሪካ የጦር መሳሪያዎችን ሕዋ ላይ ልትገጥም ነው

AMN- ግንቦት 20/2017 ዓ.ም

አሜሪካ የጦር መሳሪያዎችን ሕዋ ላይ ለመግጠም በዝግጅት ላይ መሆኗን ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ተናግረዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ሀገራቸውን ከየትኛውም የዓለም ክፍል ሊፈጸም ከሚችል ጥቃት ለመጠበቅ፣ የሚሳኤል መከላከያን ጨምሮ ሌሎች የጦር መሳሪያዎችን በሕዋ ላይ እንደሚገጥሙ አስታውቀዋል፡፡

ትራምፕ በሕዋ ላይ የሚገነባውን የሃይፐርሶኒክ፣ የባሊስቲክ እና የመርከብ ሚሳኤሎች መቃወሚያ ሥርዓት ንድፍን በትናንትናው ዕለት ማጽደቃቸውንም ገልጸዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ “ሀገራችንን ከውጪ የሚሳኤል ጥቃት መከላከል የሚያስችል እጅግ የተራቀቀ የሚሳኤል ጋሻ በሕዋ ላይ እንደምገነባ ለአሜሪካ ህዝብ ቃል እገባለሁ” ብለዋል፡፡

በዓለም ታሪክ የመጀመሪይው መሆኑ የተነገረው የፕሬዚዳንቱ ከሕዋ ላይ ጦር የመታጠቅ ዝግጅት፣ ትራምፕ ከዚህ ቀደም ይፋ ያደረጉት የጎልደን ዶም ዕቅዳቸው አካል መሆኑን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

ትራምፕ በብዙ ቢሊየን ዶላር በጀት ‘ጎልደን ዶም’ የተሰኘ የተቀናጀ የሚሳኤል ጥቃት ምላሽ ሰጪ የጦር ስርዓት ሕዋ ላይ እገነባለሁ ማለታቸው አይዘነጋም፡፡

በኢዮብ መንግስቱ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review