የአዲስ አበባ ከተማ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለከተማዋ ዕድገት እየሰጡ ላሉት በሳል አመራር እውቅና ሰጥቷል፡፡
የጋራ ምክር ቤቱ ለከንቲባ አዳነች አቤቤ እውቅናውን የሰጠው የአዲስ አበባን ህዝብ ኑሮ በተጨባጭ የለወጡ ግዙፍ የልማት ስራዎችን ከጎበኙ እና ከከንቲባዋ ጋር በጋራ ጉዳዮች ዙሪያ ከተወያዩ በኋላ ነው።
የጋራ ምክር ቤቱ መሪዎች ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና መላው አመራራቸው የከተማዋን ዘላቂ ልማትን ታሳቢ ያደረጉ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት እና በጥራት በማከናወን ህዝቡን ተጠቃሚ ማድረግ በመቻላቸው ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል፡፡
ሁሉም ኢትዮጵያዊያን የፖለቲካ ልዩነቶቻቸውን በማክበር ለሀገር ሰላምና ልማት በጋራ መስራት እንዳለባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።