AMN ሐምሌ 23/2018

የአፍሪካ ሀገራት እርስ በእርስ፣ ከሩሲያ እና ከተቀረው ዓለም ጋር ያላቸውን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማጠናከር ያለመውና በአህጉሩ የመጀመሪያው የሆነው “ወርልድ ፐብሊክ ሰሚት አፍሪካ 2026” (World Public Summit Africa 2026) በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።

መቀመጫውን በሞስኮ ያደረገው “ወርልድ ፒፕልስ አሴምብሊ” ከግሎባል ብላክ ሴንተር ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የዚህ ጉባኤ አካል የሆነ “የአንድነት ድምፅ” የተሰኘ የኪነ-ጥበብ ዝግጅትም የመላው ጥቁር ህዝብ ኩራት፤ የጽናት ተምሳሌት በሆነው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ተካሂዷል፡፡
በመድረኩ ላይ ከ16 የአፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ የኪነ-ጥበብ ባለሞያዎች ተሳትፈዋል።

በሕዝብ ለሕዝብ ዲፕሎማሲ የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ 10 አፍሪካውያንም ልዩ እውቅና ተሰጥቷል፡፡

ጉባዔዉ የአፍሪካ ሃገራትን እና የጥቁር ህዝቦችን አቋም እና የውሳኔ ሃሳብ አሰንዶ በመስከረም ወር በሞስኮ ለሚካሄደው 2ኛው ዓለም አቀፍ የሕዝብ ጉባኤ እንዲሁም በጥቅምት ወር ለሚደረገው 3ኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ዋና የመነሻ ሀሳቦችን ማቅረብን አላማው አድርጎ የተዘጋጀ ነዉ።

ዓለም እየተቀየረች ባለችበት በዚህ ወቅት አፍሪካ በለውጡ ላይ የራሷን ተፅእኖ ማበርከት እንድትችል መንገድ የሚከፍት መሆኑ መገለጹ የአድዋ ድል መታሰቢያ ለኤኤምኤን የላከዉ መረጃ ያመላክታል።