ጠቅላይ ሚኒስትሩ በይፋዊ የፌስቡክ ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት “ዛሬ የተመለከትናት ጂግጂጋ ባለፈው ጥር ከተመለከትናት ይዞታዋ በሚታይ መልክ የተቀየረች ናት” ብለዋል።
በመላው ከተማዋ በሺሆች የሚቆጠሩ አዳዲስ መኖሪያ ቤቶች እየተገነቡ ሲሆን በኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች በሁሉም አካባቢ የመኖሪያ ሁኔታን በግልጽ እያሻሻሉ ይታያሉ ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ።
የከተማ ማዕከሎቻችንን ስናዘምን የምንገነባው ለዛሬ ብቻ ሳይሆን ለነገም መሠረት እያኖርን መሆኑን መገንዘብ ይገባናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ርዕያችን እንደኢትዮጵያዊ እና አፍሪካዊ ጠቃሚ በሆኑልን ጉዳዮች ላይ የተተከለ መሆኑን ማስታወስ ይገባናልም ብለዋል።
በዚህ መንፈስ የሶማሌ ክልል በቱሪዝም አዳዲስ እድሎችን እየከፈተ እነዚህ ደሚገኝ ጠቅሰዋል። ወደ መጠናቀቂያ ምዕራፍ በደረሰው የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት ለምስራቁ የሀገራችን ክፍል አዲስ ዋጋ የጨመረ እድል እየፈጠረ መሆኑን ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአጠቃላይም የተመለከትነው የሥራ እድገት በጂግጂጋ እና በመላው ክልሉ የሚስተዋለውን መነቃቃት የሚገልጽ ነው ብለዋል።