ኢሬቻ ምስጋና እና አብሮነት የሚጸናበት በዓል ነው

You are currently viewing ኢሬቻ ምስጋና እና አብሮነት የሚጸናበት በዓል ነው

AMN መስከረም 23/2018

ኢሬቻ ምስጋና እና አብሮነት የሚጸናበት በዓል ነው ሲሉ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ።

7ኛው የኢሬቻ ፎረም በቢሾፍቱ ከተማ ሆረ ሀርሴዴ አዳራሽ “ኢሬቻ ለሀገር ማንሰራራት” በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ ይገኛል።

በፎረሙ ላይ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ ቤልጂጌ (ዶ/ር)፣ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት

ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማን፣ ሚኒስትሮች፣ የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ አባ ገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በመድረኩ ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት በክልሉ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ በሁሉም ዘርፎች ውጤታማ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት እየተከናወኑ የሚገኙ ወሳኝ ሀገራዊ የልማት ስራዎች ለመጪው ጊዜ መሠረት የሚጥሉ መሆናቸውንም ጠቁመዋል።

የባህል እሴቶችን በማጉላት ለቱሪዝም ዘርፉ ከፍታ እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረው፤ ኢሬቻ የሰላም፣ የምስጋና እና አብሮነት የሚጸናበት በዓል ነው ማለታቸዉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል ነገ መስከረም 24 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሆራ ፊንፊኔ እንዲሁም ከነገ ወዲያ እሑድ መስከረም 25 ቀን 2018 ዓ.ም በቢሾፍቱ ሆራ ሀርሰዲ “ኢሬቻ ለሀገር ማንሰራራት” በሚል መሪ ሀሳብ ይከበራል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review