በአርሰናል ጥሩ ጊዜ እያሳለፈ የሚገኘው ዳቪድ ራያ ደሞዙን የሚያሻሽልለት ውል ቀርቦለታል፡፡
ስፔናዊ ግብጠባቂ እስከ 2028 የሚቆየው ውል እንደተጠበቀ ሆኖ ደሞዙ ግን እንደሚጨምርለት ቢ ቢ ሲ ስፖርት ዘግቧል፡፡

ራያ በ2023 ነበር ከብሬንትፎርድ አርሰናልን የተቀላቀለው፡፡ የ30 ዓመቱ ግብ ጠባቂ በአርሰናል የሚያገኘው ደሞዝ በሳምንት 100 ሺ ፓውንድ እንደሆነ ዘገባው አስታውሷል፡፡
በሸዋንግዛው ግርማ