ኢትዮጵያ ቀይ ባህርን ለማጣት የወሰደባትን 30 ዓመት ወደ ቀይ ባህር ለመመለስ ሌላ 30 ዓመት አያስፈልጋትም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ

You are currently viewing ኢትዮጵያ ቀይ ባህርን ለማጣት የወሰደባትን 30 ዓመት ወደ ቀይ ባህር ለመመለስ ሌላ 30 ዓመት አያስፈልጋትም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ
  • Post category:ፖለቲካ

AMN ጥቅምት 19/2018

ኢትዮጵያ ቀይ ባህርን ለማጣት የወሰደባትን 30 ዓመታት ወደ ቀይ ባህር ለመመለስ ሌላ 30 ዓመታት አያስፈልጋትም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባ በተካሀደበት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሰላምና ጸጥታን በሚመለከት በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ፣ ኢትዮጵያ ቀይ ባህርን ለማጣት የወሰደባትን 30 ዓመታት ወደ ቀይ ባህር ለመመለስ ሌላ 30 ዓመታት አያስፈልጋትም ብለዋል።

የቀይ ባህር ጉዳይ ህጋዊ፣ ታሪካዊ፣ መልክዓ ምድራዊ(ጂኦግራፊያዊ) እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ጥያቄ እንደሆነ እናምናለን ሲሉም ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ቀይ ባህርን ለማጣት 30 ዓመት በላይ ያህል የወሰደ ትግል እንደነበር ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ሀገሪቱ ወደ ቀይ ባህር ለመመለስ 30 ዓመት አያስፈልጋትም ነው ያሉት።

ይህን ጉዳይ ለመፍታት በተረጋጋ፣ በሰከነ እና በውይይት መሄድ አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመው፤ ለማጣት የፈጀውን ያህል ለመመለስ አይፈጅብንም ሲሉም በአጽንኦት ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ የባህር በር ያጣችበት መንገድ የኢትዮጵያ ህዝብም ሆነ ካቢኔ ያልወሰነው፣ ተወካዮች ያላዩት መሆኑን ጠቁመው፤ ጥያቄው ይህን ትልቅ ጉዳይ ማን ወሰነው ብሎ መጠየቅ ተገቢ መሆኑን አስረድተዋል።

ኢትዮጵያ የባህር በር ያጣችበት መንገድ ህጋዊ እና ተቋማዊ መሠረት የሌለው እንደሆነም ነው የገለጹት።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review