“መገናኛ ብዙኃን በኢጋድ ቀጠና ሰላም፣ መረጋጋትና ውሕደት ለማስፈን ወሳኝ አጋር ናቸው” – ጌድዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር)

You are currently viewing “መገናኛ ብዙኃን በኢጋድ ቀጠና ሰላም፣ መረጋጋትና ውሕደት ለማስፈን ወሳኝ አጋር ናቸው” – ጌድዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር)
  • Post category:ፖለቲካ

AMN – ሕዳር 21/2018 ዓ.ም.

የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጌድዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) በ3ኛው የኢጋድ መገናኛ ብዙኃን የሽልማት ሥነ-ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር፣ መገናኛ ብዙኃን የአፍሪካ ቀንድ ዕድገትን ለመቅረጽ ወሳኝ አጋር መሆናቸውን ገልጸዋል።

ጋዜጠኞች በቀጠናው ታሪኮችን በመቅረጽ፣ መግባባትን በማሳደግ እና የመቋቋም አቅምን በመገንባት የማይተካ ሚና እንደሚጫወቱ ያላቸውን ዕምነት ሚንስትሩ አረጋግጠዋል።

“መገናኛ ብዙኃን በቀጠናው ጉዳዮች ተራ ታዛቢ ሳይሆኑ፣ ለሰላማዊ፣ ብልጽግናዊ እና ዘላቂ የአፍሪካ ቀንድ ሰላም ወሳኝ አጋር ናቸው። ጋዜጠኞች የእውነት ጠባቂዎች በመሆን፣ ዜጎች ለተሻለ ውሳኔ እንዲበቁ መረጃዎችን ያቀርባሉ” ብለዋል።

ኢጋድ በአሁኑ ወቅት በአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ፣ ዓለም አቀፍ የፀጥታ ስጋቶች፣ መፈናቀልና ፍልሰትን የመመከት ኃላፊነት ፊቱ መደቀኑን ሚንስትሩ ገልጸዋል።

የዘንድሮው ሽልማት “ደኅንነቱ የተጠበቀ፣ የማይበገርና የተረጋጋ ክልል እንዲኖረን ስለአየር ንብረት ለውጥ ተግባር እንናገር!’ በሚል መሪ ሀሳብ መካሄዱ ተገቢ ነው” በማለት ተናግረዋል።

ሚንስትሩ ጋዜጠኞች የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የተደረጉ ጥረቶችን፣ አዳዲስ የአመቺነት ዘዴዎችን እና የሰብዓዊነት ዋጋን የሚያሳዩ ታሪኮችን በመንገር ፖሊሲ አውጪዎችን እንዲያግዙ አጽንዖት ሰጥተዋል።

#ኢጋድመገናኛብዙኃን (IGAD Media)

#ኢጋድሽልማት (IGAD Award)

#IGADMediaAwards

#HornOfAfrica

#JournalismForPeace

#ClimateActionHoA

#DrWorknehGebeyehu

#AMN

#EthiopianAirForce

#Ethiopia

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review