በመደመር መንግሥት ውስጥ የሽግግር ትስስር በሦስት ነገሮች ላይ ያተኩራል!

You are currently viewing በመደመር መንግሥት ውስጥ የሽግግር ትስስር በሦስት ነገሮች ላይ ያተኩራል!
  • Post category:ፖለቲካ

AMN – ሕዳር 21/2018 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመደመር መንግሥት ውስጥ የሽግግር ትስስር በሦስት ነገሮች ላይ እንደሚያተኩር ገለጹ።

ጠቅላይ ሚንስትሩ እነዚህን ሦስት የሽግግር ትስስሮች ሲያብራሩ፣ የመጀመሪያው መንደርደሪያ፣ ሁለተኛው መሻገሪያ እንዲሁም ሦስተኛው መስፈንጠሪያ ናቸው ብለዋል።

• መንደርደሪያው አቅምን ከችግር ማላቀቅ እንደሆነ፣

• መሻገሪያው ደግሞ መደላድልና መሠረት መጣል እንደሆነ ያብራሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣

• መስፈንጠሪያው ደግሞ ማሳለጥን እና ማስተሳሰርን የሚያካትት እንደሆነም አስረድተዋል።

ከተማና ግብርና አቅምን ከችግር ማላቀቂያ መንደርደሪያ ሲሆኑ፣ ቱሪዝምና ማዕድን ደግሞ መሸጋገሪያ መደላድል የሚፈጥሩ እንደሆኑና ኢንዱስትሪ መስፈንጠሪያ እንዲሁም ዲጂታል ደግሞ ማስተሳሰሪያ መሆናቸውን ተናግረዋል።

እነዚህን ነገሮች በአዲስ ራዕይና አስተሳሰብ አስተሳስረን መምራት ከተቻለ ብልጽግናን በአጭር ጊዜ እናረጋግጣለን ብለዋል ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ።

በአስማረ መኮንን

#የመደመርመንግስት

#የዘርፎችእመርታ

#ብልጽግናፓርቲ

#AbiyAhmed

#ዐቢይአሕመድ

#የአመራሮችስልጠና

#AMN

#AddisAbaba

#Ethiopia

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review