ፍርድ ቤቱ ለሚዲያው ግልጋሎት የሚውሉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን አበርክቷል።
አዲስ ሚዲያ ኔት ዎርክ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ካሉ ተቋማት ጋር በቅንጅት ይሰራል። ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ የአዲስ አበባ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት አንዱ ነው።
የአዲስ አበባ ይግባኝ ሰሚፍርድ ቤት ከኤኤም ኤን ጋር በጋራ እየሰራ ነው ያሉት የፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት አቶ ተስፋዬ መለሰ ፍርድ ቤቱ በቀጣይም ከሚዲያው ጋር የበለጠ ተቀራርቦ ለመስራት ቁርጠኛ ስለመሆኑም አንስተዋል።

የግብዓት ስጦታውም የተቋማቱን መልካም ግንኙነትና አብሮ የመስራት ፍላጎት የሚያሳድግ ነውም ብለዋል። የተበረከተው ስጦታም ለሚዲያው የድምፅና ምስል አገልግሎት የሚውሉ ግብዓቶች ስለመሆናቸው ተነስቷል።
የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የሚዲያ ቴክኖሎጂ ዘርፍ አማካሪና ምክትል ስራ አስፈፃሚ አቶ ፍፁም አረዳ ስጦታው ሚዲያው ለሚሰጠው አገልግሎት ከፍ ያለ እገዛ አለውም ብለዋል።
ፍርድ ቤቱ ለሚዲያው ያደረገው ስጦታ በተቋማቱ መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያጠናክር ስለመሆኑም አንስተዋል። ግብዓቶቹም ለተቋሙ አገልግሎት ተጨማሪ ጉልበት የሚሆኑ ናቸውም ብለዋል አቶ ፍፁም።
በፂዮን ማሞ