የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ በማለፉ ለቡድኑ አባላት እና ለኢትዮጵያ ሕዝብ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ እንኳን ደስ አለን! በማለት ባሰፈሩት መልእክት በእግር ኳስ ስፖርት የጀመርነው ፕሮጀክት ፍሬ በማፍራት ላይ ነው ብለዋል፡፡
ዛሬ በመዲናችን አዲስ አበባ ሲካሄድ በነበረው የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ አገራት ከ17 ዓመት በታች ውድድር፣ ብሔራዊ ቡድናችን የኬንያ አቻውን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት በመርታት ከ 22 ዓመታት በኋላ ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፍ ችሏል።
ይህ ድል የእግር ኳስ ስፖርት ወዳድ ለሆነው ህዝባችን የዘመናት ቁጭት በቅርቡ መልስ እንደሚያገኝ ያሳየ ነው ብለዋል፡፡
ቀይ ቀበሮዎቹ ያስመዘገቡት ውጤት ለዘርፉ የሰጠነው ትኩረት ውጤት እያፈራ መሆኑን ማሳያ ነው።
በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም መላው የቡድኑ አባላትን፣ የኢትዮዽያን ሕዝብ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ ብለዋል፡፡