በ14ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ መርሃግብር ከብሬንትፎርድ ጋር የተጫወተው አርሰናል 2ለ0 አሸንፏል። የመድፈኞቹን ግቦች ሚካኤል ሜሪኖ እና ቡካዮ ሳካ ከመረብ አሳርፈዋል።
የሰሜን ለንደኑ ክለብ ድሉን ተከትሎ በ33 ነጥብ መሪነቱን አስቀጥሏል። አርሰናል በቀጣይ የፊታችን ቅዳሜ አስቶንቪላን ይገጥማል።
በሌሎች ጨዋታዎች አስቶንቪላ ብራይተንን 4ለ3 ረቷል። ክሪስታል ፓላስ በርንሌይን ፣ ኖቲንግሃም ፎረስት ደግሞ ወልቭስን በተመሳሳይ 1ለ0 አሸንፈዋል።
በሸዋንግዛው ግርማ