በሮድ ሬስ የብስክሌት ውድድር ለገሰ ሰለሞን ሁለተኛ ሆኖ በማጠናቀቅ የብር ሜዳሊያ ለሀገሩ አስገኝቷል።
ለገሰ ሰለሞን ከውድድሩ በኋላ ለኤ ኤም ኤን በሰጠው አስተያየት በአጭር ጊዜ ዝግጅት ጠንካራ ተፎካካሪ በመሆን ለሀገሩ ሜዳሊያ በማምጣቱ ደስተኛ እንደሆነ ተናግሯል።
አሰልጣኙ ዮናስ ዘርዓብሩክ በበኩሉ በውጤቱ ደስተኛ መሆኑን ተናግሮ በቀጣይ ከዚህ የተሻለ ለማስመዝገብ እንሰራለን ሲል ገልጿል።
በውድድሩ አልጄሪያ በቀዳሚነት ስታጠናቅቅ ቱኒዚያ በሶስተኛነት ጨርሳለች።
ኢትዮጵያ በ4ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ኦሎምፒክ በ6 ወርቅ በ6ብር እና 5 ንሃስ በማግኘት ጠንካራ ፉክክር እያደረገች ትገኛለች።
በአለማየሁ ሙሳ