ሐሰተኛ መታወቂያ በመያዝ የዘረፋና ዕገታ ወንጀል የፈጸሙ ተከሳሾች በጽኑ እስራት ተቀጡ

You are currently viewing ሐሰተኛ መታወቂያ በመያዝ የዘረፋና ዕገታ ወንጀል የፈጸሙ ተከሳሾች በጽኑ እስራት ተቀጡ

AMN – ታኅሣሥ 8/2018 ዓ.ም

የብሔራዊ ደህንነት አገልግሎት ሰራተኞች ነን በማለት ሐሰተኛ መታወቂያ በመያዝ የዘረፋና ዕገታ ወንጀል የፈጸሙ በጽኑ እስራት ተቀጡ።

‎አንደኛ ተከሳሽ አንተነህ በላይ የሐሰተኛ መታወቂያ ስሙ ብሩክ ሽመልስ ሁለተኛ ተከሳሽ ሚኪያስ አመኑ ሐሰተኛ የመታወቂያ ስሙ አማን ወርቁ ከአንደኛ ተከሳሽ ጋር ከሰበታ ከተማ መኪና ተከራይተው ሐሰተኛ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት መያዣ ትዕዛዝ ይዘው በአዳማ ከተማ ወንጀል ለመፈጸም መንቀሳቀሳቸው ተገልጿል ፡፡

የከሳሾቹ ሁኔታዎችን ከአጣሩ በኋላ ወንጂ ወረዳ ፉአድ ሸምሱ የተባለ መኖሪያ ቤት በመሄድ ሐሰተኛ የብሔራዊ ደህንነት አገልግሎት መታወቂያ በማሳየት የግል ተበዳይ ፉአድ ሸምሱን በሕግ ትፈለጋለህ በማለት በያዙት ህገ-ወጥ ሽጉጥ አስፈራርተው ወደ ተከራዩት መኪና በማስገባት አግተው ለማምለጥ ሞክረዋል፡፡

በወቅቱ ተበዳዩ ባሰማው የድረሱልኝ ጩኸት የአካባቢው ማህበረሰብ መንገድ በመዝጋት ተጠርጣሪዎቹን ነሐሴ 16 ቀን 2017 ዓ.ም በቁጥጥር ሥር በማዋል ለአዳማ ከተማ የደበላ ክፍለ ከተማ ፖሊስ አሳልፈው ሰጥተዋል፡፡

የደበላ ክፍለ ከተማ ፖሊስም በተከሳሾቹ ላይ የምርመራ መዝገብ ከፍቶ ለዓቃቢ ሕግ በመላክ፤ ዓቃቢሕግም የፖሊስን መረጃና ማስረጃ ተቀብሎ የምርመራ መዝገብ በማደራጀት በአዳማ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ መስርቷል።

የአዳማ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም የቀረበውን መረጃ እና ማስረጃ መርምሮ ጥፋተኞችን ያርማል ሌሎችንም ያስተምራል በማለት ህዳር 17 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በ1ኛ ተከሳሽ አንተነህ በላይ ላይ የ10 ከ8 ወር ቅጣት እንዲሁም በ2ኛ ተከሳሽ ሚኪያስ አመኑ ላይ ደግሞ የ9 ዓመት ከ8 ወር ጽኑ እስራት እዲቀጡ መወሰኑን የኢፌፖሚ ለኤ ኤም ኤን በላከው መረጃ ገልጿል ።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review