ኒውካስትል ዩናይትድ ከ ማንችስተር ሲቲ ፡-የካራባኦ ካፕ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ

You are currently viewing ኒውካስትል ዩናይትድ ከ ማንችስተር ሲቲ ፡-የካራባኦ ካፕ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ

AMN ጥር 5 ቀን 2018 ዓ.ም

ኒውካስትል ዩናይትድ በካራባኦ ካፕ የግማሽ ፍፃሜ የመጀመሪያ ጨዋታ ማንችስተር ሲቲን ያስተናግዳል፡፡ የባለፈው ዓመት የውድድሩ አሸናፊ ኒውካስትል በሩብ ፍፃሜው ፉልሃምን 2ለ1 ባመሸነፍ ነው ግማሽ ፍፃሜ የደረሰው፡፡

ማንችስተር ሲቲ በበኩሉ ብሬንትፎርድን 2ለ0 በመርታት ለዛሬው ጨዋታ በቅቷል፡፡ ሁለቱ ክለቦች በዘንድሮ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያ ዙር ግንኙነታቸው ኒውካስትል 2ለ1 ማሸነፉ ይታወሳል፡፡

የውድድሩን ዋንጫ በማንሳት ረገድ ማንችስተር ሲቲ የተሸለው ክለብ ነው፡፡ ውሃ ሰማያዊ ለባሾቹ ስምንት ጊዜ ባለድል መሆን ችለዋል፡፡ ከዚህ ውስጥ አራቱን ያገኙት በፔፕ ጋርዲዮላ እየተመሩ ነው፡፡

ኒውካስትል ዩናይትድ በአንፃሩ ባለፈው ዓመት ሊቨርፑልን አሸንፈው ካነሱት ዋንጫ ውጪ ሌላ አላሳኩም፡፡ ዋንጫው ከ70 ዓመት በኋላ ያገኙት እንደነበር ይታወሳል፡፡

በሴንት ጀምስ ፓርክ የሚደረገው የኒውካስትል እና ማንችስተር ሲቲ ጨዋታ ምሽት 5 ሰዓት ላይ ይጀምራል፡፡ የመልሱ ጨዋታ ከሦስት ሳምንታት በኋላ በኢትሃድ ስታዲየም ይከናወናል፡፡

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review