የጋራ ሀገራዊ ትርክት መፍጠር አለመቻል ደካማ ተቋማዊ ቅቡልነት፣ የመከፋፈልና የመውደቅ አዙሪት ሊያስከትል ይችላል

You are currently viewing የጋራ ሀገራዊ ትርክት መፍጠር አለመቻል ደካማ ተቋማዊ ቅቡልነት፣ የመከፋፈልና የመውደቅ አዙሪት ሊያስከትል ይችላል
  • Post category:ፖለቲካ

AMN – ጥር 05 ቀን 2018 ዓ.ም

“የጋራ ሀገራዊ ትርክት መቅረፅ አስፈላጊነትና ተቋማዊ አቀራረብ” ላይ ትኩረት አድርጎ በጅማ ከተማ የተካሄደው ሀገር አቀፍ ጉባኤ “የጅማ ስምምነትን” በማፅደቅ ተጠናቋል።

ከጥር 4 እስከ 5 ቀን 2018 ዓ.ም በጅማ ከተማ የተካሄደው ሀገር አቀፍ ኮንፈረንስ የተለያዩ ጥናታዊ ፅህፎችና የውይይት ሰነዶች ቀረበውበት የጅማ ስምምነትን በማፅደቅ ተጠናቋል።

የጋራ ሀገራዊ ትርክት ግንባታ ለኢትዮጵያ አስፈላጊ መሆኑ በስምምነት መግለጫው የተመላከተ ሲሆን የጋራ ሀገራዊ ትርክት አለመፍጠር ደግሞ ደካማ ተቋማዊ ቅቡልነት፣ የመከፋፈልና የመውደቅ አዙሪት ሊያስከትል እንደሚችል አመላክቷል።

ለጋራ ሀገራዊ ትርክት ግንባታ ተቋማዊ ቅርፅ መስጠት፣ የአሰራር መርሆዎችን ማዘጋጀት እና የተቋማትን ኃላፊነቶች መበየን እንደሚያስፈልግም በስምምነት መግለጫው ተነስቷል።

የስልጡንና ሰላማዊ ፖለቲካ ማዕከል (ሴንተር ፎር ሪስፖንሲብል ኤንድ ፒስፉል ፖለቲክስ) ከኦሮሚያ ክልል እና ጅማ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ባዘጋጁት ሀገር አቀፍ ኮንፈረንስ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ ምሁራን፣ የሚዲያና ኪነጥበብ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

በካሳሁን አንዱዓለም

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review