የጥምቀት በዓል ኢትዮጵያ በአደባባይ የምትደምቅበት ውድ ጌጧ መሆኑን የኢፌዴሪ ምትክል ጠቅላይ ሚንስትር ገለጹ

You are currently viewing የጥምቀት በዓል ኢትዮጵያ በአደባባይ የምትደምቅበት ውድ ጌጧ መሆኑን የኢፌዴሪ ምትክል ጠቅላይ ሚንስትር ገለጹ

AMN – ጥር 10/2018 ዓ.ም.

የኢፌዴሪ ምትክል ጠቅላይ ሚንስትር ለከተራ እና ለጥምቀት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ጥምቀት ፍቅርንና ትኅትናን የምንማርበት ልዩ በዓል ነው። በሰማይም በምድርም የከበረው ኢየሱስ ክርስቶስ ዝቅ ብሎ በፍጡሩና በአገልጋዩ እጅ ተጠመቀ ብለዋል።

ኢትዮጵያ የልጆቿን እርስ በርስ መፋቀር፣ በአንድነትና በአብሮነት መኖር ዘወትር ትሻለች። ፍቅር ኃይላችን፣ አቅማችንና የአንድነት ካስማችን ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ መምህረ ትኅትና ነው። በጥምቀት ፈጽሞ ያሳየን የትኅትና አምላክነቱን ነው። በፍጡሩ የሁሉ ባለቤትና ንጉሥ ሆኖ ሳለ በአገልጋዩ በዮሐንስ እጅ መጠመቁ ትኅትናን ሊያስተምረን ነው በማለት ገልጸውታል።

እኛም ትኁታን ልንሆን፣ ያለንበት ቦታ፣ የሀብት መጠን፣ የዝና ልክ፣ የኃይል ጥንካሬ ሳይወስነን ዝቅ ብለን ሕዝባችንን ልናገለግል ያስፈልጋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ አሁን የሚያስፈልጋት ጭቃ ነክተው፣ አፈር ረግጠው፣ አቧራዋን አራግፈው ወደ ልዕልና ለማሻገር የሚሠሩላትን መሆኑን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያም በትጉኃን ልጆቿ የብዙ ዓመታት መከራዋን እየገፈፈች፣ ሥር የሰደዱ ችግሮቿን እየፈታች፣ ወደ አዲስ ምዕራፍ በመሻገር ላይ ትገኛለች። ከዕዳዋ የሚልቀውን ሀብቷን እየገለጠች ወደ ምንዳ እየቀየረች ነው።

የጥምቀት በዓል ኢትዮጵያ በዐደባባይ የምትደምቅበት ውድ ጌጧ ነው። በዓሉ ኢትዮጵያውያን ኅብረረ ብሔራዊ አንድነታቸውን የሚገልጡበት ነው፡፡ ይህን የፍቅርና የአንድነት መገለጫና የዓለም ቅርስ የሆነውን በዓል ጠብቆ ማቆየት የእኛው ኃላፊነት ነው ብለዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review