AMN-ጥር 17/2018 ዓ.ም
ለኢትዮጵያ አየር ኃይል ሰማይ ወሰን ሆኖ አያውቅም፤ የጀግንነት አሻራውን የሚያሳርፍበት፣ ብቃቱን የሚለካበትና የሀገርን ኩራት የሚያውጅበት ሰፊ የመጫወቻ ሜዳው ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትሰስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት ሰማዩ የኛ ነው የሚል መርሁን በኩራት ለዘጠና ዓመታት አውጇል። 90 ከቁጥር በላይ ነው የምንለው በምክንያት ነው ብለዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ዘጠኝ አሥርት ዓመታት የታተመ የማይበገር የአየር ክልልን የማስጠበቅ ፅናት፣ በሰማይ ላይ የተጻፈ የሉዓላዊነት ታሪክ፣ ዘመን የተሻገረ የነጻነትና የአንድነት አርማ ነው ብለዋል፡፡