አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በይዘት አቀራርብ፣ በቴክኖሎጂና በሰው ሀብት ልማት ግንባታ አመርቂ ለውጥ አምጥቷል- አቶ ካሳሁን ጎንፋ

You are currently viewing አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በይዘት አቀራርብ፣ በቴክኖሎጂና በሰው ሀብት ልማት ግንባታ አመርቂ ለውጥ አምጥቷል- አቶ ካሳሁን ጎንፋ

AMN- ጥር 22/2018 ዓ.ም

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ባለፉት 6 ወራት ያከናወቸናቸውን ተግባራት ከአመራሩ እና ከሰራተኛው ጋር ገምግሟል፡፡ ባለፉት ስድስት ወራት በከተማ አቀፍ እና በሀገር አቀፍ ጉዳዮች ላይ ውጤታማ የሆኑ ሥራዎች መከናወናቸው ተገልጿል፡፡

የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ እንደገለጹት ሚዲያው በይዘት አቀራርብ፣ በቴክኖሎጂ እና በሰው ሀብት ልማት ግንባታ ለውጥ አምጥቷል፡፡ ሚዲያው የህዝብ ጥያቄዎች የሚንሸራሸሩበት፣ የአገልግሎት አሰጣጥ እና የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲፈቱ የሚያስችሉ መድረኮች መፍጠሩን ዋና ስራ አስፈፃሚው ገልጸዋል፡፡

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ተወዳዳሪ፣ ተመራጭ እና ቀዳሚ የሜትሮፖሊታን ሚዲያ መሆን የሚያስችለውን ስትራቴጂ በመንደፍ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ሚዲያው ባለፉት 6 ወራት በተለይ በቴክኖሎጂ አቅም ከፍተኛ የሆነ ለውጥ ማምጣቱን የገለጹት አቶ ካሳሁን፣ በቀጣይም በሁሉም አማራጮች አዳዲስ ይዘቶችን በመተግበር ተደራሽነቱን እንደሚያሰፋም ጠቅሰዋል፡፡

የተቋሙን የ6 ወራት አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡት የስትራቴጂክ ሥራ አመራር ልማትና ፈጠራ ዳይሬክተር አቶ አበበ ደሳለ፤ ሚዲያው ባለፉት 6 ወራት ስኬታማ ተግባራትን ማከናወኑን ገልጸዋል።

በከተማዋ የተከናወኑ የኮሪደር ልማት እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ሥራዎች ለሕዝብ ይበልጥ እንዲተዋወቁ መደረጉን በሪፖርቱ አንስተዋል። በጎ አድራጎት፣ አረንጓዴ አሻራ፣ ሕዝባዊ እና ሃይማኖታዊ በዓላት በቀጥታ ሥርጭት ለተመልካች ተደራሽ ሆነዋል።

ከማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችጋር በተገናኘም፤ በኑሮ ውድነት፣ በአገልግሎት አሰጣጥ፣ በገቢ አሰባሰብ እና በከተማ ጽዳት ዙሪያ ትኩረት ሰጥቶ በመሥራት ውጤት ተመዝግቧል ብለዋል። በአጠቃላይ በግማሽ ዓመቱ በሁሉም የሥርጭት አማራጮች በተሰራው ስራ በርካታ ውጤታማ የሆኑ ፕሮግራሞች ለሕዝብ መቅረባቸውን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው፣ በቀረበው ሪፖርት ዙሪያ አስተያየት የሰጡ ሲሆን፣ ተቋሙ በቴክኖሎጂ ራሱን ለማዘመን ያሳየውን እድገት አድንቀዋል፡፡ በሰው ኃይል አደረጃጀት በኩልም እየተሰራ ያለው ሥራ ትልቅ ተቋማዊ አቅም መፍጠሩንም ገልጸዋል፡፡

በቀጣይም ባለፉት 6 ወራት በስኬት የተመዘገቡ ተግባራትን በማስቀጠል እና በክፍተት የተስተዋሉ ችግሮችን በመቅረፍ ተቋሙ የላቀ ተወዳዳሪ ለመሆን እያደረገ ያለውን ጥረት በሙሉ አቅማቸው ለመደገፍ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በአስማረ መኮንን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review