ለሀገራዊ ምክክር ጉባኤው የተለዩ አጀንዳዎች በምን መስፈርት ተመረጡ?

You are currently viewing ለሀገራዊ ምክክር ጉባኤው የተለዩ አጀንዳዎች በምን መስፈርት ተመረጡ?

AMN – ግንቦት 14/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለሀገራዊ ምክክር ጉባኤው የለያቸውን አጀንዳዎች ለሃይማኖት ተቋማትና ለሲቪክ ማኅበራት አቅርቦ የግብዓት ማሰባሰብ ሥራ አከናውኗል።

ዛሬ ግንቦት 14 ቀን 2018 ዓ.ም በተካሄደው በዚህ መድረክ ላይ፣ አጀንዳዎቹ የተቀረፁበትን ዋና ዋና መሥፈርቶች የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አምባዬ ኦጋቶ (ዶ/ር) ለተሳታፊዎቹ በዝርዝር አብራርተዋል።

ኮሚሽነር አምባዬ (ዶ/ር) እንዳብራሩት፤ የአጀንዳዎቹ መመረጥ በዘፈቀደ ሳይሆን ሀገሪቱ ያሉባትን ስር የሰደዱ ችግሮች በዘላቂነት መፍታት በሚያስችሉ 10 ዋና ዋና መስፈርቶች ላይ የተመሠረተ ነው።

የቀረቡት አጀንዳዎች ለጉባኤው ብቁ የሆኑት የሚከተሉትን መስፈርቶች አሟልተው ሲገኙ መሆናቸውንም ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

* የጉዳዩ ጭብጥ የህገ-መንግስት ማሻሻልን የሚያስከትል ከሆነ

* ጉዳዩ በሀገሪቱ ያሉ ለዘመናት ሲንከባለሉ የመጡ የአለመግባባት መንስኤዎችን እና ችግሮችን በትክልል የሚዳስስ እና በጉዳዩ ላይ መመካከር ችግሩን በትክክል የሚፈታ

* ጉዳዩ ላይ ምክክር ቢደረግበት በህዝብ እና በሕዝብ መካከል ያሉትን ግንኙነቶች በማሻሻል መተማመንን የሚፈጥር

* አዲስ የፖለቲካ ስርዓት ለመፍጠር የሚረዳ ጉዳይ

* ጉዳዩ ላይ ምክክር ቢደረግበት በህዝብ እና በመንግስት መካከል ያሉትን ግንኙነቶች በማሻሻል መተማመንን የሚፈጥር

* የዲሞክራሲ ስርዓት እንዲገነባ ለማስቻል አስተዋጽኦ የሚያደርግ

* ቅቡልነት ያለው ሀገረ-መንግስት በመገንባት ሂደት ጠንካራ መሰረት ለመጣል የሚያግዝ

* የሰላም ግንባታ፡- ወቅታዊ ችግሮችን ዘላቂ በሆነ መንገድ በመፍታት አስተማማኝ ሰላም ለመፍጠር የሚያግዝ

* ለሀገራዊ መግባባት አስተዋጽ የሚያደርግ

* የተሸረሸሩ ሀገራዊ እሴቶችን ለማደስ አስተዋጽዖ የሚያደርግ ሊሆኑ እንደሚገባ ከኮሚሽኑ የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review