ኢጋድ እና ጣሊያን የአፍሪካን ሰላምና ብልጽግና ለማረጋገጥ አጋርነታቸዉን እንደሚያጠናክሩ ገለጹ

You are currently viewing ኢጋድ እና ጣሊያን የአፍሪካን ሰላምና ብልጽግና ለማረጋገጥ አጋርነታቸዉን እንደሚያጠናክሩ ገለጹ
  • Post category:አፍሪካ

AMN ጥር 27/2018

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ኢጋድ እና ጣሊያን የአፍሪካን ሰላምና ብልጽግና ለማረጋገጥ አጋርነታቸዉን እንደሚያጠናክሩ ገልጸዋል።

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ኢጋድ (IGAD) ዋና ጸሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ(ዶ/ር) በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር እንዲሁም በጅቡቲ፣ በደቡብ ሱዳንና በኢጋድ ተቀዳሚ መልክተኛ ከሆኑት አምባሳደር ሴም ፋብሪዚ ጋር ተወያይተዋል።

ውይይቱ አሁን ባለው የቀጠናው የሰላምና የደኅንነት ሁኔታ እንዲሁም ጣሊያን የኢጋድ አጋሮች ፎረም ሰብሳቢ በመሆን በምትጫወተው ሚና ላይ ያተኮረ ነው።

ውይይቱ በአዲስ አበባ በሚካሄደው የጣሊያን-አፍሪካ ጉባኤ ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ በዚህም ጉባኤ ላይ ኢጋድ የቀጠናዊ ትብብርና የልማት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች ለማሳደግ በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ይሳተፋል።

ጣሊያን እ.ኤ.አ. ከ1986 ጀምሮ የቆየ ታሪካዊ አጋር እንደመሆኗ መጠን፣ ኢጋድ በቀጠናው መረጋጋትን፣ ሁሉን አቀፍ ሰላምን እና ዘላቂ ልማትን ለማምጣት የሚያደርገውን ጥረት መደገፏን መቀጠሏን ኤኤምኤን ከኢጋድ ያገኘዉ መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review