ከ39ኛው የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ከ50 በላይ የጎንዮሽ ውይይቶች ተካሂደዋል

You are currently viewing ከ39ኛው የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ከ50 በላይ የጎንዮሽ ውይይቶች ተካሂደዋል
  • Post category:አፍሪካ

AMN- የካቲት 8/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ ሲካሄድ የቆየው 39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ በስኬት ተጠናቋል።

የጉባኤውን መጠናቀቅ ተከትሎ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ የሱፍ እና የህብረቱ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በጉባኤው አበይት አጀንዳዎች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።

መሪዎቹ ሰላምን በማረጋገጥ አህጉሪቱን የተፈጥሮ እና የሰው ኃይል ሀብት በመጠቀም ለእድገት መስራት እንደሚቻል መክረዋል።

ከዋናው የህብረቱ ጉባኤ ጎን ለጎን በቢዝነስ ፈጣሪዎች፣ በውሃ ሀብት ጠበብቶች እና በጤና ዘርፍ ላይ ትኩረት ያደረጉ ከ50 በላይ የጎንዮሽ ውይይቶች መካሄዳቸው ተገልጿል፡፡

ቅኝ ግዛትን እና እሳቤውን ለመግታት በሚያስችሉ ጉዳዮች፣ እንዲሁም አፍሪካ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንድታገኝ በሚያስችሉ መንገዶች ላይ ጥልቅ ምክክር ተደርጓል።

የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ የሱፍ፣ ለጉባኤው ሁለንተናዊ ስኬታማነት ለተደረገው ርብርብ የኢትዮጵያን መንግስት እና ህዝብ አመስግነዋል።

በተመስገን ይመር

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review