AMN የካቲት 10/2018
በብልጽግና ፓርቲ አመራርነትና በዜጎች ተሳትፎ የተከናወኑት የልማት ስራዎች በክልሉ ተጨባጭ ውጤት ማስገኘታቸውን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ተናገሩ።
የብልጽግና ፓርቲ የጠቅላላ ምርጫ መወዳደሪያ የምርጫ ምልክት (የስንዴ ነዶ) እና ማኒፌስቶ ይፋ ማድረጊያ መርሃግብር በአሶሳ ከተማ ተካሂዷል።
ርዕሰ መስተደድሩ አሻድሊ ሀሰን በወቅቱ እንደተናገሩት፤ በክልሉ በብልጽግና ፓርቲ አመራርነትና በዜጎች ተሳትፎ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ በርካታ የልማት ተግባራት ተከናውነዋል።
በክልሉ የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ በተደረጉ ጥረቶች በኢኮኖሚ እና በመልካም አስተዳደር ስኬታማ ስራ መከናወኑን ገልጸው፤ በዚህም ተጨባጭ ውጤት ተመዝግቧል ማለታቸዉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡