AMN – የካቲት 19/2018 ዓ.ም
የሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ቀዌሳ (ሮባ ቀዌሳ) የ20ኛ ዓመት የዕረፍት መታሰቢያ እንዲሁም የሥነ-ጥበብ ሥራዎቻቸውና ማህበራዊ አስተዋጽኦዎቻቸው፣ በተወለዱበት አምቦ ወረዳ ጎረምቲ ቀበሌ፣ በእሳቸው ስም በተሰየመው የኢፋ ቦሩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተካሂዷል።
መርሃ-ግብሩ በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር እና በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ትብብር የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።
በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የፌዴራል፣ የክልልና የወረዳ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ አባ ገዳዎች፣ አደ ሲንቄዎች፣ አርቲስቶች፣ መምህራን፣ ተማሪዎችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ሎሬት ፀጋዬ (ሮባ ቀዌሳ) በሥነ-ጽሑፍ ሥራዎቻቸው ከአገር አልፈው በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅናን ያተረፉ ግለሰብ ሲሆኑ፤ አምቦ ዩኒቨርሲቲ ለእሳቸው መታሰቢያ የሚሆን የባህል ጥናትና ምርምር ማዕከል በማቋቋም በሥነ-ጽሑፍ የነቃ ትውልድ የማፍራት ሥራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።
ሎሬት ፀጋዬ እስከ 1998 ዓ.ም በሞት እስከተለዩበት ጊዜ ድረስ፣ እሳቸውንም ሆነ ኢትዮጵያን የሚያስተዋውቁ ትልልቅ ሥራዎችን በአገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ደረጃ አከናውነዋል።
በቶለሳ መብራቴ