AMN -የካቲት 26/2018 ዓ.ም
በሴንት ጀምስ ፓርክ ኒውካስትል ዩናይትድን የገጠመው ማንችስተር ዩናይትድ 2ለ1 ተሸንፏል። ኒውካስትል ዩናይትድ አንቶኒ ጎርደን በፍፁም ቅጣት ምት ባስቆጠረው ግብ መምራት ቢችልም ፣ ካሲሜሮ ዩናይትድን አቻ አድርጓል።
ነገር ግን ኒውካስትል ተቀይሮ በገባው ዊሊያም ኦሱላ ግሩም ግብ ጨዋታውን በድል ተወጥቷል። የኤዲ ሃው ቡድን ይህን አስደናቂ ድል ያሳካው ጃኮብ ራምሴን 45ኛው ደቂቃ ላይ በሁለት ቢጫ በቀይ ካርድ አጥቶ ነው።
ኒውካስትል ለአራት ተከታታይ ዓመት ማንችስተር ዩናይትድን በሜዳው ማሸነፍም ችሏል። የዩናይትዱ አሰልጣኝ ማይክል ካሪክ ከሰባት ጨዋታ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ተሸንፏል።
ቀያይ ሰይጠናቱ ምንም እንኳን ቢሸነፉም በ51 ነጥብ ባሉበት 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።
በሸዋንግዛው ግርማ