አርሰናል ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቀለ

You are currently viewing አርሰናል ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቀለ

AMN- የካቲት 28/2018 ዓ.ም

በእንግሊዝ ኤፍ ኤ ካፕ 5ኛ ዙር የሦስተኛ ዲቪዚዮን (ሊግ 1) ተወዳዳሪው ማንስፊልድ ታውንን የገጠመው አርሰናል 2ለ1 አሸንፏል።

በማንስፊልድ ሜዳ ፊልድ ሚል በተደረገው ጨዋታ ኖኒ ማዱኤኬ አርሰናልን ቀዳሚ ማድረግ ችሏል።

ለፕሪምየር ሊጉ መሪ በቀላሉ እጃቸውን ያልሰጡት ማንስፊልዶች ዊል ኢቫንስ ባስቆጠረው ግብ አቻ መሆን ችለው ነበር።

ተቀይሮ የገባው ኤብሬቺ ኤዜ የአርሰናልን አሸናፊነት ያረጋገጠች ግብ አስቆጥሮ ጨዋታው 2ለ1 ተጠናቋል።

መድፈኞቹም ከስድስት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የኤፍ ኤ ካፕ ሩብ ፍፃሜ ተፋላሚ ሆነዋል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review