በዓለም ላይ የምርጫ ካርድ በመውሰድና ድምጽ መስጠት የተሻለ የምርጫ ተሳትፎ ያላቸዉ ቀዳሚ ሃገራት

You are currently viewing በዓለም ላይ የምርጫ ካርድ በመውሰድና ድምጽ መስጠት የተሻለ የምርጫ ተሳትፎ ያላቸዉ ቀዳሚ ሃገራት

AMN መጋቢት 2/2018 ዓ.ም

ምርጫ ጠንካራ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት በመገንባት ሂደት ዉስጥ ያለዉ ተሳትፎ የላቀ ነዉ፡፡

በርካታ የአለም ሃገራት ግልጽ፤ ተአማኒና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ በማካሄድ የተሻለ ሃገር መገንባት ችለዋል፤ የምርጫ ተሳትፎአቸዉንም አሳድገዋል፡፡

የምርጫ ተሳትፎአቸዉ እንደ የምርጫው ወቅትና እንደ አገሪቱ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ የተለያየ ቢሆንም ድምጽ መስጠት በሕግ ግዴታ ከሆኑባቸው አገራት መካከል ቤልጂየም፤ አውስትራሊያ እና ሉክሰምበርግ የምርጫ ካርድ በመውሰድና ድምጽ መስጠት የላቀ ተሳትፎ አላቸዉ፡፡

በፈቃደኝነት ደምጽ በመስጠት ከፍተኛ ተሳትፎ ካላቸዉ ሃገራት መካከል ደግሞ ስዊድን፤ዴንማርክ ፤ ኖርዌይ እና ኡራጓይ ተጠቃሾች ናቸዉ፡፡ ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር ካላቸው የአለም ሃገራት መካከል ደግሞ ህንድ፤ ኢንዶኔዥያ እና ብራዚል በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ፡፡

በአፍሪካ በከፍተኛ የመራጮች ምዝገባ ከሚታወቁት ሃገራት መካከል ናይጄሪያ፤ ኢትዮጵያ፤ ግብፅ፤ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ደቡብ አፍሪካ የተሻለ ተሞክሮ አላቸዉ፡፡

በናይጄሪያ እ.ኤ.አ በ2023 በተደረገው ምርጫ ከ93 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለምርጫ ተመዝግበው ነበር።

በኢትዮጵያ ለ6ኛው አገራዊ ምርጫ ከ38 ሚሊዮን በላይ ህዝብ የምርጫ ካርድ መውሰዱ ይታወሳል።\ በሰሜን አፍሪካ ግብፅ ከፍተኛ ቁጥር ያለው መራጭ የያዘች ሃገር ስትሆን በቅርብ ጊዜያት በተደረጉ ምርጫዎች ከ60 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለመምረጥ ተመዝግበዋል።

በአንዳንድ ሃገራት ምዝገባው ዲጂታል መሆኑ ትክክለኛውን ቁጥር ለማወቅ የሚረዳ ሲሆን ኢትዮጵያም በምርጫ ታሪክ ዉስጥ ለመጀመሪያ በ7ኛዉ ጠቅላላ ምርጫ ዲጂታል የመራጮች ምዝገባን በተመረጡ አካባቢዎች በማከናወን ላይ ትገኛለች፡፡

በወንድማገኝ አሰፋ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review