ነዳጅ ከተተመነለት የዋጋ መጠንና የግብይት ሰንሰለት ውጪ በሚሸጡ ሕገወጦች ላይ የተጠናከረ እርምጃ መውስድ ተጀምሯል- አሕመድ ሽዴ

You are currently viewing ነዳጅ ከተተመነለት የዋጋ መጠንና የግብይት ሰንሰለት ውጪ በሚሸጡ ሕገወጦች ላይ የተጠናከረ እርምጃ መውስድ ተጀምሯል- አሕመድ ሽዴ

AMN- መጋቢት 2/2018 ዓ.ም

በመንግሥት ከፍተኛ ድጎማ የሚቀርበውን ነዳጅ ከተተመነለት የዋጋ መጠንና የግብይት ሰንሰለት ውጪ በሚሸጡ ሕገወጦች ላይ የተጠናከረ እርምጃ መውስድ መጀመሩን የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ አስታወቁ።

የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ በነዳጅ አቅርቦት ዙሪያ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ፤ መንግሥት በዓለም ተለዋዋጭ የገበያ ሁኔታ ውስጥ የህዝብን ጫና ለመቀነስ በቢሊየን የሚቆጠር ዶላር ድጎማ እያደረገ ነው ብለዋል።

በዚህም መንግሥት ነዳጅን ለኅብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ በየዓመቱ ከ4 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ በመመደብ እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።

በትናንትናው ዕለት የተደረገውን የዋጋ ማስተካከያም መንግሥት ነዳጅ ከሚገዛበት የዓለም ገበያ ዋጋ አንጻር ሲታይ እጅግ ዝቅተኛ መሆኑን ተናግረዋል።

መንግሥት በከፍተኛ ቁርጠኝነት የሚያቀርበው ነዳጅ በተቀመጠለት የዋጋ ተመንና የግብይት ሰንሰለት እየተሸጠ አለመሆኑን በጥናት እንደተረጋገጠ ገልጸዋል።

በዚህም ምክንያት በኅብረተሰቡ ላይ ያልተገባ ጫና በሚፈጥሩ ሕገ-ወጥ አካላትና ተባባሪዎቻቸው ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመሩንና ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።

ኅብረተሰቡም እንዲህ ያሉ ሕገ-ወጥ ድርጊቶችን በመጠቆም እንዲተባበር ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በመካከለኛው ምስራቅ ካለው ወቅታዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞ የአቅርቦት መስተጓጎል እንዳይፈጠር መንግሥት የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም አስተማማኝ አቅርቦት እንዲኖር እየሠራ መሆኑም ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review