የግብርና ምርት መሸጫ ማዕከላት የኑሮ ውድነቱን በማረጋጋት ረገድ የሚጠበቅባቸውን ሚና እየተወጡ ነው

You are currently viewing የግብርና ምርት መሸጫ ማዕከላት የኑሮ ውድነቱን በማረጋጋት ረገድ የሚጠበቅባቸውን ሚና እየተወጡ ነው

AMM- መጋቢት 4/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አማካኝነት በተለያዩ ክፍለ ከተሞች የተገነቡት ዘመናዊ የግብርና ምርቶች መሸጫ ማዕከላት፣ ጥራት ያላቸውን ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ለህብረተሰቡ ትልቅ እፎይታ እየሰጡ እንደሚገኙ ተገለጸ።

በተለይም በለሚ ኩራ እና በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተሞች የሚገኙት እነዚህ ማዕከላት ሥራ ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ፣ የኑሮ ውድነቱን በማረጋጋት ረገድ የሚጠበቅባቸውን ሚና እየተወጡ መሆናቸው ተመልክቷል።

ማዕከላቱ ጤፍን ጨምሮ እንደ ቲማቲም፣ ሽንኩርት፣ ድንችና ካሮት ያሉ መሠረታዊ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን በስፋት ለገበያ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ።

በእነዚህ የገበያ ስፍራዎች ኤ ኤም ኤን ያነጋገራቸው ሸማቾች እንደገለጹት፣ በማዕከላቱና በመደበኛው የችርቻሮ ገበያ መካከል ያለው የዋጋ ልዩነት እጅግ ሰፊ ነው።

ለአብነትም በመደበኛው ገበያ ከ70 እስከ 80 ብር የሚሸጡ ምርቶች በማዕከላቱ ውስጥ ከ40 እስከ 60 ብር ባለው ዋጋ እየቀረቡ ይገኛሉ ሲሉ ገልጸዋል።

የዋጋ ማረጋጋቱ በዋናው የፍጆታ ምርት በጤፍ ላይም በግልጽ እየታየ መሆኑን ሸማቾች ገልጸዋል።

በግለሰብ ወፍጮ ቤቶችና በተለያዩ የገበያ ስፍራዎች በኪሎ እስከ 145 ብር የሚሸጠው የጤፍ ምርት፣ በእነዚህ ማዕከላት እንደ ጥራቱ ደረጃ ከ113 እስከ 115 ብር ባለው ዋጋ ለሸማቹ እየቀረበ ይገኛል።

ይህም ነዋሪው በአንድ ኪሎ ጤፍ ላይ ብቻ ከ20 እስከ 30 ብር የሚደርስ ቅናሽ እንዲያገኝ አስችሎታል ሲሉ ሸማቾች ተናግረዋል።

ይህ ውጤት ሊገኝ የቻለው ምርቱ በቀጥታ ከአምራች ገበሬዎች ለሸማቹ እንዲቀርብ በመደረጉ ሲሆን፣ ይህም በገበያው ላይ ቢያንስ የ15 በመቶ የዋጋ ቅናሽ እንዲፈጠር አድርጓል።

የለሚ ኩራ የግብርና ምርት መሸጫ ማዕከል ሥራ አስኪያጅ አቶ ገነነ ፈጠነ እንደተናገሩት፤ ከዋጋው ተመጣጣኝነት ባሻገር፣ የማዕከላቱ አስተባባሪዎች የምርቶቹን ጥራትና ትኩስነት በየቀኑ በጥብቅ ይከታተላሉ።

ይህም ህብረተሰቡ ጤናማና ጥራት ያለው ምርት እንዲያገኝ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን አስታውቀዋል።

በበረከት ጌታቸው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review