የሴኔጋል የአፍሪካ ዋንጫ ውጤት ተሰርዞ ዋንጫው ለሞሮኮ እንዲሰጥ ተወሰነ

You are currently viewing የሴኔጋል የአፍሪካ ዋንጫ ውጤት ተሰርዞ ዋንጫው ለሞሮኮ እንዲሰጥ ተወሰነ

AMN- መጋቢት 8/2018 ዓ.ም

ካፍ በሴኔጋል አሸናፊነት የተጠናቀቀውን 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውጤት መሰረዙን እና ዋንጫው ለሞሮኮ እንዲበረከት መወሰኑን ይፋ አድርጓል።

በከፍተኛ ውዝግብ ታጅቦ የተጠናቀቀውን የአፍሪካ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ ሴኔጋል አዘጋጇ ሞሮኮን 1ለ0 ማሸነፏ ይታወሳል።

በወቅቱ በጨዋታው ጭማሪ ደቂቃ ላይ ለሞሮኮ ፍፁም ቅጣት ምት ሲሰጥ የተበሳጩት የሴኔጋል የቡድን አባላት ሜዳ ለቀው ወጥተው ነበር።

ጉዳዩን ሲመረምር የቆየው ካፍ የቡድን አባላቱ ወደ ሜዳ ተመልሰው ጨዋታውን ቢጨርሱም አቋርጠው መውጣታቸው ለቅጣት ዳርጓቸዋል።

የካፍ ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ የሞሮኮን ቅሬታ ሰምቶ መተዳደሪያ ደንቡን በመጥቀስ የፍፃሜ ጨዋታው ውጤት ፎርፌ ሆኖ በሞሮኮ 3ለ0 አሸናፊነት እንዲመዘገብ ወስኗል።

በውዝግብ ታጅቦ የተጠናቀቀው የፍፃሜ ጨዋታ ሁለት ወር አልፎትም አነጋጋሪነቱ ቀጥሏል።

የሴኔጋል እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሚሰጠው ምላሽ እና ሞሮኳዊያን ደስታቸውን እንዴት እንደሚገልፁ ማየት ያጓጓል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review