AMN – መጋቢት 13/2018 ዓ.ም
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ”ቅድሚያ ለሴቶች!” በሚል መሪ ሃሳብ ባሰፈሩት መልዕክት ”ሴቶች በጥበብ ይኖራሉ፤ በራስ መተማመን ይሠራሉ፤ በራስ መተማመን ይሮጣሉ፤ ይችላሉም! ሁላችንም እጅ ለእጅ ተያይዘን የአገራችንን ብልፅግና እናረጋግጣለን ሲሉ ገልጸዋል።
ዛሬ ማለዳ 16 ሺህ ሴቶች የሚሳተፉበትን የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በድምቀት አስጀምረናል።

በታላቁ ሩጫ አዘጋጅነት በየዓመቱ የሚካሄደው ይህ ውድድር፤ ዘንድሮ በኮሪደር ልማታችን አማካኝነት እጅግ ውብ፣ ምቹ እና ለከተማችን አዲስ ዘመናዊ መልክ ባላበሰው በቦሌ – አትላስ – ኡራኤል መንገድ ላይ በልዩ ድምቀት ተከናውኗል ብለዋል።
እንኳን ደስ አላችሁ! ሁላችሁም አሸናፊዎች ናችሁ ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት አስተላልፈዋል።