የሴቶች የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ረገድ ከፍተኛ ስኬት ተገኝቷል- ኤርጎጌ ተስፋዬ

You are currently viewing የሴቶች የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ረገድ ከፍተኛ ስኬት ተገኝቷል- ኤርጎጌ ተስፋዬ

AMN-ሚያዝያ 20/2018 ዓ.ም

የሴቶች የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ረገድ ከፍተኛ ስኬት መገኘቱን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ተናገሩ።

ሚኒስትሯ ባለፉት ስምንት የለውጥ ዓመታት በሚኒስቴር መስሪያቤታቸው የተመዘገቡ ዐበይት ስኬቶችን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት አቅርበዋል። ‎

በዚህም ዘርፉ ከለውጡ በፊት ሲቸገርበት የነበሩ መጠነ ሰፊ ክፍተቶችን በመለየት ፈጣን መፍትሔ በመስጠት ሰፊ ስኬቶችን አስመዝግቧል።

ከተገኙ ስኬቶች መካከል የፖሊሲና የህግ ማዕቀፎችን በማዘጋጀት የዜጎችን መብት ጥበቃ፣ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፣ አደረጃጀቶችን በመደገፍና በማጠናከር መብትና ግዴታ በማወቅ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፣ የአቅመ ደካማ ዜጎችን የመደገፍና የማገዝ ባህል ማሳደግ ጥቂቶቹ ናቸው። ‎

እነዚህ ስኬቶች ቁጥር ብቻ ሳይሆኑ በተጨባጭ 4 ሚሊየን 330 ሺህ 948 የሚሆኑ ወጣቶች እና 26 ሚሊየን 845 ሺህ 686 ሴቶች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የተቻለበት ትልቅ ስኬትም ተጠቃሽ ነው፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የሴቶችንና ወጣቶችን የፖለቲካ ተሳትፎን ከማሳደግ አኳያ ሰፊ ስራ ተሰርቶ ተጨባጭ ስኬቶች ተመዝግበዋል። ‎

በተጨማሪም ዘርፉ ካስመዘገባቸው ስኬቶች መካከል የማህበራዊ አገልግሎት ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ አንዱና ዋነኛው ሲሆን በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋ ተጋላጭ ሆነው ድጋፍ የተደረገላቸው ዜጎች፣ ከጎዳና ላይ የተነሱ ዜጎች፣ የተሀድሶ አገልግሎት ያገኙ አካል ጉዳተኞች፣ በማህበረሰብ እንክብካቤ ጥምረቶች የተሰበሰበ ሀብት ዋነኞቹ ስኬቶች መሆናቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review