የቅዱስ ሲኖዶስ የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ በቤተ ክርስቲያኗ ጉዳዮች ላይ በመወያየት ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቀቀ

You are currently viewing የቅዱስ ሲኖዶስ የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ በቤተ ክርስቲያኗ ጉዳዮች ላይ በመወያየት ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቀቀ

AMN ግንቦት 6/2018

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ወቅታዊና ወሳኝ ሐዋርያዊና ቀኖናዊ በሆኑ የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች ላይ በመወያየት ለቤተ-ክርስቲያኗ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ዛሬ ተጠናቅቋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በዓመት ሁለት ጊዜ ጉባኤ ያደርጋል። የመጀመሪያው ጉባኤ በጥቅምት የሚደረግ ሲሆን፤ ሁለተኛው ርክበ ካህናት ጉባዔ በዓለ ትንሣኤ በዋለ በበዓለ ሃምሳ እኩሌታ በዕለተ ረቡዕ የሚጀመረው ነው።

በዚህም የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ከሚያዝያ 28 ቀን 2018 ዓም ጀምሮ ሲካሄድ የቆየ ሲሆን፤ ዛሬ ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ.ም ረፋድ ላይ ተጠናቅቆ መግለጫ ተሰጥቷል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስትያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ጉባኤው በዋነኝነት በሀገር ሰላም በቤተክርስትያን አንድነት ሰለሰው ልጆች ሁሉ ክብርና አንድነት እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ ሲካሄድ መቆየቱ ገልፀዋል።

ጉባዔው ወቅታዊና ወሳኝ ሐዋርያዊና ቀኖናዊ በሆኑ የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ለቤተ-ክርስቲያኗ እና ለሀገር ጠቃሚ የሆኑ ውሳኔዎችን በማሳለፍ መጠናቀቁን መግለጻቸዉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review