አዲስ አበባ የለውጥ ህልሞቻችንን በትጋት በማሳካት ለትውልድ የምትመች ከተማ ሆናለች -ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ

You are currently viewing አዲስ አበባ የለውጥ ህልሞቻችንን በትጋት በማሳካት ለትውልድ የምትመች ከተማ ሆናለች -ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ

AMN- ግንቦት 7/2018 ዓ.ም

አዲስ አበባ የለውጥ ህልሞቻችንን በትጋት በማሳካት ለትውልድ የምትመች ከተማ ሆናለች ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት በመዲናችን አዲስ አበባ የተከናወነው ዓለምን ያስደመመ ለውጥ በብዕር ተከትቦ፣ ለታሪክ ማጣቀሻነት በሚበቃ መልኩ የቀረበበትንና በዓለም አቀፍ ምሁራን የተዘጋጀውን ድንቅ መጽሐፍ በደማቅ ሥነ ሥርዓት መርቀናል ብለዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም መጽሐፉ የሁላችንም ታሪክ ነው፤ እናንብበው፣ የለውጥና የስኬት ታሪካችንንም ለዓለም እናጋራ ሲሉ በአጽንኦት መልክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review