የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት የምርቶችን የጥራት ደረጃ በኦንላይን ማረጋገጥ የሚያስችል መተግበሪያ ይፋ አደረገ

You are currently viewing የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት የምርቶችን የጥራት ደረጃ በኦንላይን ማረጋገጥ የሚያስችል መተግበሪያ ይፋ አደረገ

AMN ግንቦት 13/2018

የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት የምርቶችን የጥራት ደረጃ በኦንላይን ማረጋገጥ የሚያስችል መተግበሪያ ይፋ አድርጓል።

መተግበሪያው የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) እና የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር መሠረት በቀለ (ዶ/ር) በተገኙበት ተመርቆ ወደ ስራ ገብቷል።

የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር መሠረት በቀለ (ዶ/ር)፥ መተግበሪያው ምርቶችን በኦንላይን ስርዓት በመለየትና በመተንተን የጥራት ደረጃቸውን ማረጋገጥ እንደሚያስችል ገልጸዋል።

ይህ መተግበሪያ ህብረተሰቡ ያለምንም መጭበርበር ምርቶችን እንዲሸምት እንደሚያስችል ጠቁመዋል።

ይህ የዲጂታላይዜሽን ስርዓት የኢትዮጵያን የምርትና አገልግሎት ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት እንደሚጨምር ተናግረዋል።

ወቅቱን የዋጀ የደረጃ ትግበራ ስራዎችን በጥራትና ፍጥነት ተደራሽ ለማድረግ አይነተኛ ሚና እንደሚኖረውም እንዲሁ።

መተግበሪያውን ማንኛውም ሰው ከአፕ ስቶር ወይም ፕላይ ስቶር አውርዶ በመመዝገብ መጠቀም እንደሚችል ገልጸዋል።

የኦንላይን መተግበሪያው አስተማማኝነት በሚመለከተው አካል መረጋገጡን ጠቁመዋል።

ኢንስቲትዩቱ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ያከናወናቸውን አጠቃላይ ተቋማዊ የሪፎርም ስራዎችንም ማስመረቁን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review