የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የበጀት አመቱ ከመጠናቀቁ በፊት እንዲካሄድ ከፍተኛ ዝግጅት እየተደረገ ነው – የኢትዮጵያን ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

You are currently viewing የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የበጀት አመቱ ከመጠናቀቁ በፊት እንዲካሄድ ከፍተኛ ዝግጅት እየተደረገ ነው – የኢትዮጵያን ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

AMN – ግንቦት 14/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሀገራዊ ምክክር አጀንዳ ማሰባሰብ መርሀ ግብር ከሀይማኖት ተቋማት እና ከሲቢክ ማህበራት ድርጅቶች ጋር እያካሄደ ነው።

የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የበጀት አመቱ ከመጠናቀቁ በፊት እንዲካሄድ ከፍተኛ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያን ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ተናግረዋል፡፡

ኮሚሽኑ በሀገሪቱ የሚታዩ የፖለቲካ እና የሀሳብ አለመግባባቶችን ለመፍታት ተቋቁሞ ላለፉት አራት አመታት ከሁለት ወራት አጀንዳ የማሰባሰብ ስራዉን አካታች እና ፍትሀዊ በሆነ መንገድ እያከናወነ መሆኑን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ አስታውቀዋል።

በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደቱ የሀይማኖት ተቋማትና የሲቪክ ማህበራትን ጨምሮ ሁሉምን የህብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽ ለማድረግ ከፍተኛ ሚና እንደነበረው አስታውሰዋል።

ኮሚሽኑ ወገንተኝነቱን ለህዝብ በማድረግ 93 በመቶ የሀገሪቱን ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮችን ተደራሽ ያደረገ ሲሆን ቀሪዎቹን በቀጣይ ለማዳረስ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ኮሚሽነሩ አንስተዋል።

ለምክክር ሂደቱ የፓለቲካ ፓርቲዎች፣ ምሁራን፣ ታዋቂ ሰወች እንዲሁም የሀይማኖት ተቋማትና የሲቢክ ማህበራት በንቃት መሳተፍቸውን የገለፁት ፕሮፌሰሩ በሂደቱ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን እና የመፍትሄ እርምጃዎችን አብራርተዋል።

የተሰበሰቡ አጀንዳዎችን ወደ ዲጅታል ስርአት የመሰነድ ስራዎች እየተጠናቀቁ መሆኑንም ነው ኮሚሽነሩ ለውይይት መነሻ ባቀረቡት ሰነድ ላይ ያብራሩት።

የሲቪክ ማህበራት ፕሬዚዳንት አህመድ ሁሴን፣ የሲቪክ ማህበራት ሰላም የሚረጋገጠው በህዝብ ንቁ ተሳትፎ መሆኑን ያምናል፤ ልዩነቶችን በውይይት ለመፍታት እና የተሻለች ኢትዮጵያን ለመገንባት ሚናውን ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን አንስተዋል።

በቤተልሔም አየነው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review